ተጨማሪ መጠባበቂያ ተግባራዊ የተደረገበት ባንክ የለም
የብድር ክልከላ ጣሪያ ቢነሳም ባንኮች አሁንም የብድር እድገታቸው ቀደም ሲል ከነበረው ለውጥ አለማሳየቱን እና አሁንም በብድር ወደ ገበያው የሚገባው መጠን ክልከላ ከነበረበት ለውጥ አለማሳየቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡
ባንኮች ላይ እስካሁን የተጣለ የመጠባበቂያ ጭማሪ አለመኖሩንም ማእከላዊ ባንኩ አስታውቋል፡፡
የብሄራዊ ባንክ 8ኛ የገንዘብ ፖሊሲ ኮምቴ ስብሰባ እና የቦርድ ውሳኔ ጋር በተያያዘ ገዥው እዮብ ተካልኝ (ፒኤችዲ) መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ኪሚቴው ለቦርድ አስቀርቦ ካስወሰናቸው አዳዲስ የፖሊሲ ውሳኔዎች ጋር በተያያዘ ከከዚ ቀደሙ አንፃር ምንም ለውጥ ያልታየ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፡፡
ባለፈው ሀምሌ በተደረገው የ7ኛ የኮሚቴ ውሳኔ የተተገበሩ አሰራሮች እንደነበሩ መቀጠላቸው ነው የታወቀው፡፡
ሆኖም የኪሚቴ ው የግምገማ ውጤት እንዳሳው የብድር ክልከላ ቢነሳም ባንኮች አሁንም በሚያቀርቡት ብድር ላይ ጥንቃቄ የታከለበት አቅርቦት እያደረጉ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በ7ኛ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ እንደተወሰነው የብድር እድገቱን ለመቆጣጠር ባንኮች ላይ የብድር ተቀማጭ ጥመርታን መሰረት በማድረግ በተናጠል የተለየ የመጠባበቂያ ተቀማጭ እንዲተገበር ወስኖ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ሆኖም እዮብ በመግለጫቸው እንደገለጹት እስካሁን የተለየ መጠባበቂያ ተቀማጭ የተጣለበት ባንክ የለም፡፡
እንዲያም ሆኖ የብድር ተቀማጭ ጥመርታቸው ከፍ ያለባቸውን ባንኮች ማእከላዊ ባንኩ በጥንቃቄ እየተመለከተ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
የባንኮች አማካኝ የብድር ተቀማጭ ጥመርታ በ2018 በጀት አመት መጨረሻ 72.7 በመቶ ነበር፡፡ ይህም በ2016 ከነበረው 90.3 በመቶ በከፍተኛ ሁኔታ ቅናሽ የታየበት መሆኑን ብሄራዊ ባንክ ከ4 ወራት በፊት ባወጣም መግለጫ አስታወቆ ነበር፡፡
ሁሉም ባንኮች በጥንቃቄ የብድር እድገታቸውን እያከናወኑ ነው ያሉት ገዥው የብድር እድገቱ ከብድር ጣራ ክልከላ በኋላም ቢሆን ብዙ ለውጥ አላሳየም፡፡
ብሄራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል ከሶስት አመት በፊት የተለያየ የገንዘብ ፖሊሲ ምርምጃ ሲያስተዋውቅ ተግባራዊ አድርጎት በነበረው የብድር እድገት ጣራ ምክንያት በባንኮች አማካኝነት በብድር መልክ ወደገበያው የሚገባው የተጨማሪ ገንዘብ መጠን በከፍተኛ መጠን ቀንሶ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይህ ጉዳይ በባንኮች እና በንግዱ ማህበረሰብ ዘብድ መሻሻል እንዲደረግበት ጥያቄ ሲቀርብበት ነበር፡፡
የብሄራዊ ባንኩ የገንዘብ ፖለሲ ውሳኔ መረጃ እንደሚያሳየው በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ባንኮች የተጣራ የተቀማጭ ገንዘብ ክምችት 85.4 በመቶ እና አጠቃለይ የብድር ክምችት ደግሞ 42.6 በመቶ ዓመታዊ ዕድገት አስመዝግቧል፡፡
“ምንም እንኳን የብድር ዕድገት ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ (credit cap policy) ቢነሳም እና ባንኮች ከፍተኛ ቁጠባ ቢሰበስቡም፣ የሰጡት አዲስ ብድር (Disbursment) ከአጠቃላይ ተቀማጭ እና ተመላሽ አኳያ ሲነጻጸር ከባለፈው ሩብ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ተቀራራቢ ነዉ፣” ሲል ነው አክሎ የገተለጸው፡፡
አዲሱ ቀጥተኛ ያልሆነ የብድር እድገት ፖሊሲ በርካታ ባንኮችን ቀደም ሲል ተጥሎ ከነበረው የቀጥታ የፖሊሲ ቁጥጥር እድገት በበለጠ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ አሰራር እንደሆነ በባለሞያዎች ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በተመሳሳይ ኮሚቴው ባደረገው ግምገማ የመንግስት ግምጃ ቤት ሰነዶች አማካይ የወለድ ምጣኔ እንዲሁም ባንኮች እርስ በእርስ የሚበዳደሩበት የ7-ቀን የባንክ ለባንክ የገንዘብ ገበያ አማካይ የወለድ ተመኖች ከግንቦት ወር 2018 ጀምሮ ማሽቆልቆል ማሳየታቸውን ተገንዝቧል ሲል ነው ያስታወቀው፡፡
“ይሁን እንጂ የባንኮች የቁጠባ እና የማበደሪያ የወለድ ተመን ግን ከባለፈው ሩብ ዓመት መጨረሻ ለውጥ እንደሌለው ታይቷል፡፡ ሌሎች ምክንያቶች እንዳሉ ሆኖ ለአጭር ጊዜ የወለድ ተመኖች መቀነስ ባንኮች በብሔራዊ ባንክ ያላቸዉ ትርፍ ገንዘብ (excess liquidity) በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ነዉ፣” ሲል አክሏል፡፡
እንደ የግምጃ ቤት እና የጨረታ ሰነድ-ግብይት (Open Market Operations) ያሉ የገንዘብ ገበያዎች የወለድ ክፍያ ከዋጋ ግሽበት አንፃር እንዲሁም ከገበያው የማበደሪያ መጠን በከፍተኛ መጠን እየቀነሱ መምጣታቸው በገበያው እየታየ ነው፡፡
በተመሳሳይ በገያው ያለው የአቅርቦት መጠን ለመግዛት ካለው ፍለጎት አንጻር ከፍ ያለ መሆኑ ከብድር እድገት ክልከላ እና ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ አንፃር በፋይናንስ ተቋማት ከፍተኛ የገንዘብ ክምችት እንዳለ ያሳያል ሲሉ ባለሞያዎች ይገልፃሉ፡፡
የንግድ ሚዛን ጉድለት ሰፍቷል ያለው ኮሚቴው በግለሰቦች ሃዋላ (Private Transfers) እና በካፒታል ሂሳብ (Capital Account) የተመዘገበው ዕድገት አጥጋቢ በመሆኑ ለአጠቃላይ የክፍያ ሚዛን (Overall Balance of Payments) ትርፍ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡
የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከአምና ተመሳሳይ ሩብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የውጭ ሚዛን አጠቃላይ ትርፍ (Overall Surplus) በመጠኑ ቅናሽ ያሳየ ቢሆንም፣ ከሪፎርሙ በፊት ከነበረው አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱን ኮሚቴው ተገንዝቧል ሲል ነው የገለፀው፡፡
በተጨማሪም በሩብ ዓመቱ የሸቀጦች ወጪ ንግድ በተለይ የወርቅ እና የቡና አፈጻጸም አወንታዊ ዕድገት ያሳዩ ሲሆን የገቢ ሸቀጦችም እድገት ከፍተኛ ነበር፡፡


