“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!”
የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው ማዕከል ለሚድያ ባለሙያዎች የክህሎትና የስነምግባር ስልጠና ለመስጠት የተሟላ ቁመና እንዳለው የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሐይማኖት ዘለቀ ተናግረዋል::
ጋዜጠኞች የተደራጀ ስልጠና የሚያገኙበት የልቀት ማዕከል ለሚድያ ምህዳሩ በጎ ሚና ይኖረዋልም ብለዋል::
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የቦርድ ሰብሳቢ ሬድዋን ሁሴን የሚድያ ነፃነት ከኃላፊነትና ከተጠያቂነት የማይነጣጠል ነው ብለዋል::
የነፃነትና ኃላፊነትን ሚዛን ለመጠበቅ የሚድያ ልህቀት ማዕከል ትልቅ ግብአት መሆኑን ተናግረዋል::
የቦርድ ሰብሳቢው ከአምስት ጊዜ በላይ ያልተመከረ እና የእርምት ውይይት ያልተደረበት ሚድያ ላይ እርምጃ ወስደን አናውቅም ብለዋል::
አምባሳደር ሬድዋን የኃላፊነት ጥሰቶች በሚድያ ባለቤቶች እንዲሁም በባለሙያዎች እየተፈፀሙ መሆናቸውን ተናግረዋል::
ከሰሞኑ የሪፖርተር ጋዜጣ የተላለፈበት ውሳኔ መነጋገሪያ መሆኑ ይታወቃል::SECO


