ኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ገላን ወደብ መተማመኛ ሰነድ መዳረሻ ሆኖ እንዲካተት ብሔራዊ ባንክን ጠየቀ

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ገላን ሁለገብ ወደብን (GMP) ለገቢ ንግድ የባንክ መተማመኛ ሰነድ (Letter of Credit/LC) ሆኖ እንደ መዳረሻ ወደብ እንዲታወቅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥያቄ አቀረበ።

እርምጃው አዲስ የተጀመረውን የወደብ መዳረሻ አስመጪዎች በሙሉ አቅሙ እንዳይጠቀሙበት እየገደበ ያለውን የአሰራር እንቅፋት ለማስወገድ ያለመ መሆኑ ነው የተጠቀሰው።

ትላንት አርብ ህዳር 11 የባቡር ኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታከለ ኡማ ለብሔራዊ ባንክ ገዢ እዮብ ተካልኝ (ዶር) በጻፉት ደብዳቤ ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ገላን ሁለገብ ወደብ በመልቲሞዳል የትራንስፖርት ሥርዓት የሚመጡ ኮንቴይነሮችን ለማስተናገድ የሚያስፈልገው አቅም እንዳለው ማረጋገጡን ገልፆ ሌሎች የመልቲሞዳል ኦፕሬተሮች ተርሚናሉን ለደንበኞቻቸው የጭነት መዳረሻ አድርገው እንዲጠቀሙ ተፈቅዷል ሲል አስታውሷል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኅዳር 2 ቀን 2019 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በጻፈው ደብዳቤ፤ በባቡር ወደ ገላን ሁለገብ ወደብ የሚደርሱ ኮንቴይነሮች በከባድ መኪና ወደ ቃሊቲ ሳይጓጓዙ በገላን ተርሚናል በሚገኘው የጉምሩክ ጽ/ቤት የጉምሩክ ሥነ ሥርዓታቸው ተጠናቆ እንዲለቀቁ ማሳወቁን ነው የባቡር ድርጅቱ ለማእከላዊ ባንኩ በፃፈው ደብዳቤ ያሳወቀው፡፡

ይህ ውሳኔ ገላን ሁለገብ ወደብ በአሁኑ ወቅት የመልቲሞዳል ጭነቶች መዳረሻና የጉምሩክ ማስተናገጃ ሆኖ በሙሉ አቅሙ እንዲያገለግል የፈቀደ ቢሆንም ሁለገብ ወደቡ በብሔራዊ ባንክ Single Window ሥርዓት ላይ የLC መዳረሻ (final destination) ሆኖ ባለመካተቱ፤ አስመጪዎች LC ሲከፍቱ ገላንን እንደ መዳረሻ መምረጥ አልቻሉም ሲል ጠቅሷል::

“ይህ ሁኔታ ደንበኞች ከመልቲሞዳል አገልግሎቱ ሙሉ ጥቅም እንዳያገኙ፣ ተጨማሪ የትራንስፖርት ወጪና የጊዜ መጓተት እንዲደርስባቸው እያደረገ፣” ሲል ነው ያከለው፡፡

ለባንኩ የተላከው ደብዳቤ መንግሥት የሎጂስቲክስ ወጪን ለመቀነስ የያዘውን የመልቲሞዳል ትራንስፖርት ስትራቴጂ ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ገላን ሁለገብ ወደብ በSingle Window ሥርዓት ላይ የLC መዳረሻ ሆኖ እንዲካተትና ለኢትዮ ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር የመልቲሞዳል ጭነቶች ጥቅም ላይ እንዲውል እንዲፈቀድ ሲል ጠይቋል፡፡

በተጨማሪም ውሳኔውን ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በደብዳቤ በማሳወቅ በጉምሩክ ሥርዓቱም ላይ ተመሳሳይ ማስተካከያ እንዲደረግ ባንኩ ተጠይቋል፡፡SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories