ዳሸን ባንክ ከ30 ቢሊየን ብር በላይ በቴሌብር የብድር አገልግሎት ማቅረቡን አስታውቋል።
ዳሸን ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በነበረው ስራቴጂካዊ አጋርነት ባለፉት አራት ዓመታት ከ 30 ቢሊየን ብር በላይ የብድር አገልግሎት በቴሌብር በኩል ማቅረቡን ነው ዛሬ ያስታወቀው።
እስከ ኅዳር 2019 ዓ.ም በቴሌብር ላይ በሚገኙት መላ፣ መዳረሻና እንደኪሴ ከ3.4 ሚሊየን በላይ ደንበኞች የብድር አገልግሎት ባንኩ ያቀረበ ሲሆን ከ18.7 ሚሊየን በላይ የብድር ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቻለሁ ብሏል።
ዳሽን ባንክ የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ እተሰራ ያለውን ዘርፈ-ብዙ ሥራዎች ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።SECO


