በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 408 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማቅረቡን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ለኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንደገለጹት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች 408 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ቀርቧል።
የውጭ ምንዛሬው ለጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ለቆዳ፣ ለምግብና መጠጥ፣ ለኬሚካልና ኮንስትራክሽን፣ ለማኒፋክቸሪግ፣ ቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች መቅረቡን ገልጸዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል፡፡


