እዳው ከ90 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል
ከ90 ሚሊዮን ዶላር በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል እዳ ያለባት እና በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ሱዳን፤ በአንድ ዓመት ከ6 ወር እዳዋን ለመክፈል ተስማምታ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ማቋረጧን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
ወደ ጦርነት ከመግባቷ በፊት ከኢትዮጵያ ጋር የሀይል ሽያጭ ስምምነት የተዋዋለችው ሱዳን ከሁለት ዓመት በላይ ባስቆጠረው ጦርነት እዳዋን መክፈል እንዳልቻለች እና ትወስደው ከነበረው ከ120 ሜጋ ዋት ወደ 10 እና 20 ሜጋ ዋት የኃይል ፍጆታዋ ዝቅ ማለቱ መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡
በዚህም በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ያለባትን እዳ ለመክፈል ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር የመክፈያ ቀን ድርድር አድርጋ በ1 ዓመት ከ6 ወር እንድታጠናቀቅ የጊዜ ገደብ ቢሰጣትም 1 ሚሊየን ዶላር ብቻ ከፍላ ሂደቱ መቋረጡን የኃይል መስሪያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ነግረውኛልሲል አሐዱ ዘግቧል፡፡


