የኢትዮጵያ የከተማነት ምጣኔ በ5.4% እያደገ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የከተማነት ምጣኔ በ5.4% እያደገ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የከተማነት (ከተሞችን የመቀላቀል) ምጣኔ በ5 ነጥብ 4 በመቶ እያደገ እንደሚገኝ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው፣ የከተሞች እድገትና ልህቀት የአገርን አጠቃላይ ዕድገት ለመወሰን ቁልፍ እንደሆነ ባስረዳበት መድረክ ላይ መሆኑ ተጠቁሟል።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በሰጡት መግለጫ እንዳስረዱት፣ የአንድ ሀገር ዕድገትና ልህቀት የሚወሰነው በከተሞች ዕድገትና ጥራት መሆኑ የማይካድ ሀቅ ነው፡፡

ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ በከተማነት ረጅም ታሪክ ቢኖራትም፣ የነበሯት ከተሞች ታሪኳን የሚመጥን ዕድገት ሳያሳዩ መቆየታቸውንና ሀገሪቱ በከተማነት ወደኋላ መቅረቷን ገልጸዋል፡፡

ይህንን ሁኔታ ለመቀየር፣ የለውጡ መንግስት ከተሞችን ከድህነት፣ ከመልካም አስተዳደር እጦትና ከሥራ አጥነት ማሳያነት አውጥቶ፣ የብልጽግና ማሳያ ለማድረግ አቅዶ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories