የፕሬዝደንት ትረምፕ ትእዛዝን ተከትሎ አሜሪካ የሶልዲ ህትመትን አቋርጣለች

ሶልዲ/ አንድ ሳንቲም ለመቅረጽ ወይም ለማተም የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ ለመከላከል ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ያሳለፉትን ውሳኔ ተከትሎ አዳዲስ ሳንቲሞች መቀረፅ መቆሙ ትላንት በይፋ ተነግሯል፡፡

በዚህም መሰረት አሜሪካ ከ232 አመት ወዲህ ሶልዲን ወደ ገበያ ማስገባት ማቆሟ ነው የተገለፀው፡፡

ሆኖም አሁን በገበያ ውስጥ የሚገኙ ከ250 ቢሊየን በላይ ሶልዲዎች በአገልግሎት የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡

ከወራት በፊት ፕሬዝደንቱ ውሳኔውን ሲያሳልፉ አንድ ሶልዲ ለማምረት የሚወጣው ከፍጠኛ ወጪ አያዋጣም በማለት ነበር፡፡

መረጃዎች እንደሚያሳዩት አንድ ሳንቲም/ሶልዲ ለማተም አራት ሳንቲም ወጪ ይደረጋል፡፡

ከ15 አመት በፊት ኢትዮጵያ የአንድ ብር ኖት ለማሳተም የምታወጣው ወጪ እየናረ በመምጣቱ ለረጅም ጊዜ ማገልገል የሚችል ሳንቲም ማስተዋወቋ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ተደርጎ በነበረው ጥናት አንድ የአንድ ብር ወረቀጥ ገንዘብ ለማተም ከ10 ብር በላይ ወጪ ይደረግ ነበር ሆኖም ገንዘቡ ወረቀት በመሆኑ በገበያ ላይ ብዙም የማይቆይ ስለሆነ የአገልግሎት ዘመኑ አጭር በመሆኑ ወጪው ከጥቅሙ አንፃር የማያዋጣ እንደሆነ ተጠቅሶ የወረቀት ብሩን በሳንቲም መቀየር ተችሏል፡፡

ሆኖም አሁን ላይ የብር ዋጋ በከፍተኛ መጠን እየቀነሰ በመሆኑ የአንድ ብር ሳንቲም ጨምሮ ሳንቲሞች ለመገበያያ ሲውሉ አይታይም፡፡

ዘመናዊው አለም በይበልጥ ወደ ዲጂታል ግብይት እየመጣ በመሆኑ የጥሬ ገንዘብ ጥቅም እና ዝውውር በእጅጉ እየቀነሰ መሆኑም ይነገራል፡፡

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories