ዓባይ ባንክ 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር አተረፍኩ አለ

ዓባይ ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በማትረፍ በታሪኩ ከፍተኛ የሆነ ስኬት ማስመዝገቡን አስታውቋል።

የባንኩ የባለአክስዮኖች 16ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ድንገተኛ ጉባዔ ላይ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አምላኩ አስረስ (ዶ/ር) በተጠናቀቀው በጀት አመት ባንኩ የ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ገልጸዋል።
የተመዘገበው ትርፍ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ116 በመቶ ጭማሪ እንዲሁም የጠቅላላ ገቢውን በ58 በመቶ ማሳደግ ችሏል ብለዋል፡፡

የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ከባለፈው ዓመት በ36 ነጥብ 7 በመቶ በማደግ 71 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር መድረሱን ተናግረዋል፡፡

የባንኩ የተከፈለ ካፒታልም 7 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቀዋል።

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories