ቡና ባንክ አ.ማ. በ2017 የሒሳብ ዓመት ባስመዘገበው ጠንካራ የሥራ አፈጻጸም አማካይነት የካፒታል ማሳደግ ግቡን ሊያሳካ መቃረቡን አስታወቀ። ባንኩ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፣ አ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2025 ላይ የተከፈለ ካፒታሉን 5,062 ቢሊዮን ብር ማድረሱን ጠቁሟል።
ባንኩ እ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 2021 ባካሄደው 5ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔው ላይ፣ የባንኩ የተፈቀደ ካፒታል በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ 6.5 ቢሊየን ብር እንዲደርስ ውሳኔ ተላልፎ ነበር። አሁን ባለው የካፒታል መጠን፣ ቀሪው 1,437,918,400.0 ብር በዚህ የሒሳብ ዓመት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይሟላል ተብሎ ይጠበቃል።
እንደ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ የውጭ ምንዛሬ ገበያ መዋዠቅና የፖለቲካ አለመረጋጋት ባሉ ፈታኝ የሥራ አካባቢዎች መካከል ዉስጥ ቢሆንም በ2017 የሒሳብ ዓመት 1.9 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ከታክስ በኋላ ማግኘቱን አስታውቋል።
የቡና ባንክ በአሁኑ ወቅት ያለው ጠቅላላ ሀብት 65.58 ቢሊየን ብር የደረሰ ሲሆን፣ በዲጂታል ባንኪንግና ከወለድ ነፃ ባንኪንግ ዘርፍም ከፍተኛ እድገት ማስመዝገቡ ተገልጿል።


