ዛሬ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው 11ኛዉ ዙር የውጪ ምንዛሪ ጨረታ 50 ሚሊዮን ዶላር ለሽያጭ የቀረበ ሲሆን አንድ የአሜሪካን ዶላር በአማካይ ብር 154.3993 ተሸጧል።
በጨረታው 17 ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ድልድል ማግኘታቸውን ባንኩ አስታውቋል።
በ10ኛዉ ዙር ጨረታ የአንድ ዶላር አማካይ ተመን 148.1007 ብር እንደነበር ይታወሳል።
በመሆኑም ዛሬ በተደረገው የ11ኛ ጨረታ ውጤት የብር የመግዛት አቅም በ4.24 በመቶ ተዳክሟል።


