በባለሃብቶች ይነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ በመሰጠቱ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እንዲጨምር ማስቻሉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል።
በሂደት ከተመለሱ ጥያቄዎች መካከል 14 ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች መቀየር መቻሉ አንዱ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ይነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ መሆኑን ሌላ ተጠቃሽ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም ከውጭ ምንዛሪ ጋር ተያይዘው ይነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች በኢኮኖሚ ማሻሻያው መሠረት ለውጦች መገኘታቸውን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻዎችን ማስፋቱ ድርጅቶች በቀላሉ ምርታቸውን ወደ ተለያዩ ሀገራት መላክ እንዲችሉ በማድረግ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ላይ የጎላ ሚና አበርክቷል ብለዋል።
በኮሚሽኑ የሚሰጠው የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ፈጣን፣ ግልጽና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት መስጠት ማስቻሉን አመላክተዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ በአጠቃላይ በዘርፉ በተደረጉ የማሻሻያ ሥራዎች በእ.ኤ.አ 2024/2025 ከ4 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማስመዝገብ ተችሏለል።


