የገቢዎች ሠራተኞች ቪዲዮ ካሜራ የተገጠመበት ዩኒፎርም ሊለብሱ ነው

ግብር ከፋዮችን የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጣቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሠራተኞች፣ ከኅዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ካሜራ የተገጠመበት ዩኒፎርም ለብሰው እንደሚሰማሩ ተነግሯል።

እንደ ሪፖርተር ዘገባ የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ የተመደበለትን ከ1ዐዐ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በመጠቀም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት (ኢንሳ) ጋር በመቀናጀት የቦዲ ዎርን ካሜራ ፕሮጀክትን (Body Worn Camera Project) አልምቶ በማጠናቀቅ ወደ ተግባር ተሸጋግሯል።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከዛሬ ረቡዕ ኅዳር24 ጀምሮ ግብር ነክ ጉዳዮችን በተመለከተ የሕግ ማስከበርና የቁጥጥር ሥራዎችን የሚያከናውኑ ሠራተኞቹ፣ ቪዲዮ ካሜራ የተገጠመለት ዩኒፎርም በመልበስ እንደሚሰማሩ አስታውቋል።

ይህ የካሜራ ቴክኖሎጂ የቁጥጥር ባለሙያዎች ቁጥጥራቸውን በድምፅና በምሥል በመቅረፅ በቀጥታ ለዋና መሥሪያ ቤትና ለቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች እንደሚልኩ ቢሮው ገልጿል።

በመሆኑም በዋና መሥሪያ ቤትና በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የሚገኙ ባለሙያዎች፣ በቡድን የሚንቀሳቀሱ የቁጥጥር ባለሙያዎች እያንዳንዳቸው በየትኛው አካባቢ ቁጥጥር እያካሄዱ መሆናቸውን (Location Tracking)፣ እንዲሁም ከግብር ከፋዮች ጋር የሚያደርጓቸውን ንግግሮች በድምፅና በምሥል የሚከታተሉ መሆናቸውን ታውቋል።©SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories