በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኦዲት ዘርፍ ትኩረት አልተሰጠውም ተባለ

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኦዲት ዘርፍ ትኩረት አልተሰጠውም ተባለ

በሀገሪቱ 230 ብቻ የተመሰከረላቸው ሂሳብ አዋቂዎች እንዳሉ ተጠቁሟል

በኢትዮጵያ የአካውንቲንግና ኦዲቲንግ ቦርድ የተመሰከረል የሂሳብ አዋቂ የሆኑት አቶ  ጥላሁን ግርማ እንደገለጹት በኢትዮጵያ ትላልቅ የመንግስትና የግል  የፋይናንስ ተቋማት ቢገኙም የፋይናንስ ኦዲት ዘርፍ ትኩረት እንደተነፈገው ነው፡፡

በሀገሪቱ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ቢኖርም የተመሰከረላቸው ሂሳብ አዋቂዎች ቁጥር 230 ብቻ እንደሆነ  ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2014የአለም አቀፍ ሂሳብ አዘገጃጀትና አቀራረብ ስርዓት ብትቀበልም  በሂሳብ አዘገጃጀትና አቀራረብ ላይ ተለምዶአዊ አሰራር ጎልቶ ይታያል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያሉ የመንግስትና የግል ተቋማት ለዘርፉ ዝቅተኛ አመለካከት በመስጠት ባለሙያዎችን አቅም ሲያጎለብቱ እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማታቸውን ሲያዘምኑ እንደማይታዩ ገልጸዋል፡፡

ተቋማት የፋይናንስ  ተቋማቸው ማዘመን እና ለባለሙያዎች ሙያዊ ስልጠና እንዲሰጡ በህግ መገደድ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

የውጭ ባለሀብቶች ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ ትኩረት ከሚያደርጉበትና ከሚመለከቱት ውስጥ የፋይናንስ ስርዓቱ ምን  ያህል  ግልጽና ወጥነት እንዳለው መሆኑን ጠቁመው   የፋይናንስ ስራዓቱ ካልዘመነ በኢንቨስትመንት ላይ ጫናው ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አካውንቲንግና  ኦዲት ቦርድ ወደ ስራ መግባቱ በዘርፋ ቀደም ሲል ይታዩ የነበሩ ክፍተቶችን ከመሙላቱ በተጨማሪ ሁለት አይነት  ( ለባንክ የትርፍ፣ ለገቢዎች የኪሳራ ) ሪፖርት አቀራረብን ይቀርፋል ብለዋል፡፡

ቦርዱ ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን አለም አቀፍ ህጎች መቆጣተርና ተግባራዊነቱን ማረጋገጥ  እነንደሚጠበቅበት አቶ ጥላሁን ግርማ ለቅዳሜ ገበያ ተናግረዋል፡፡©SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories