ዳሸን ባንክ 50 ሺህ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ 10 ቢሊዮን ብር መመደቡን አስታወቀ

 በ2ኛው የኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያ ኮንፈረንስ  ላይ የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስፋው አለሙ ባንኩ ተጨማሪ 10 ቢሊዮን ብር መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ 50 ሺህ አርሶ አደሮችን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት አስታውቀዋል።

“ዳሸን ባንክ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን፣ “ለእርሻ” ከተሰኘ አገር በቀል ተቋም እንዲሁም ከሱፍሌት ማልት ጋር በአጋርነት የጀመረው አርሶ አደሮችን የሚደግፍ የሙከራ ፕሮጀክት ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡ ይህ ደግሞ በቀጣይ 50,000 ገበሬዎችን፣ 300 በሴቶች የሚመሩ ኢንተርፕራይዞችን እንዲሁም 10,000 ነጋዴዎችን በቀጣይ በዳሸን ሱፐር አፕ አገልግሎቶች ለማገዝ መንገድ ከፍቷል” ሲሉ አቶ አስፋው ተናግረዋል።

የዳሸን ሱፐር አፕ በተጀመረ አጭር ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ንቁ ተጠቃሚዎችን በተሳካ ሁኔታ ማፍራቱ ለባንኩ ትልቅ ተነሳሽነት መፍጠሩን ዋና ሥረሰ አስፈፃሚው አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም በአገር አቀፍ ደረጃ የኪው አር ኮድ መለያን በመጠቀም የሚደረግ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ጥሩ ውጤት ቢገኝበትም ወደሚፈለገው ደረጃ እንዳልደረሰ ሊታመን ይገባል አቶ አስፋው፣ ነገር ግን በዲጂታል መንገድ የክፍያ ስርዓቱን ለመተካት የሚደረጉት ተግባራት ተስፋ ሰጪ መሆናቸው ገልፀዋል፡፡Seco 

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories