የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) አማራ ባንክ ከወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሱ ባንኩ ከቀዳሚ የፋይናንስ ተቋማት ለመሆን በሚያደርገው ጉዞ ላይ ጤናማ አስተዳደርንና የገበያ ዲሲፕሊን መርሆዎችን ለማክበር ያስችለዋል ብለዋል፡፡
አማራ ባንክ አዳዲስ እና ደንበኛን ያማከለ የፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በአገሪቱ የካፒታል ገበያ ውስጥ ለሚኖረው ሚናና ተሳትፎ ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ሀላፊነቱን ወስዶ እንደሚሰራና የባንኩን ባለድርሻ አካላትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ብሩታዊት ዳዊት በበኩላቸው ስምምነቱ የወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ የፋይናንስና ገበያዎች ልማት ውስጥ ያለውን ሚና እንደሚያጠናክርለት ገልጸዋል፡፡
የኢንቨስትመንት ባንኩ አማራ ባንክ በባለ አክሲዮኖቹ የተያዙትን ሰነደመዋለ ነዋዮች በተቀመጠው መስፈርት መሰረት የማስመዝገብ ሂደቱን የደንበኛ ሳቢ መግለጫ (Prospectus) ማዘጋጀትን ጨምሮ ከካፒታል ገበያ ጋር የተያያዙ የማማከር ስራዎችን እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ የአማራ ባንክ አ.ማ. በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ላይ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ምዝገባ ለማካሄድ የሚያስችለውን ረቂቅ ሰነድ (Draft Prospectus) ዝግጅቱ አጠናቅቆ ለባለስልጣኑ ማስረከቡንም አስታውቀዋል፡፡
አማራ ባንክ 164 ሺህ በላይ ባለ አክሲዮኖችን ሲኖሩት ባንኩ በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 31.5 ቢሊዮን ብር ከፍ እንዳደረገ መገለጹይታወቃል፡፡@seco


