“በአገር ውስጥ ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ አጋጥሞኛል” ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድአስታውቋል፡፡
አየር ንገዱ ባወጣው መግለጫ የሚቲዎሮሎጂ መረጃ እንደሚያሳየው ይህ የአየር ፀባይ ለተወሰኑ ቀናት የሚቀጥል ነው ብሏል።
አየር መንገዱ በዚህ ምክንያት ወደተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚያደርጋቸውን በረራዎች ለማቋረጥ በመገደዱ ነው ያስታወቀው።
የአየር ፀባዩ እስከሚስተካከል እና በረራዎችን መቀጠል እስከሚቻል ድረስ መንገደኞች እንዲታገሱ ወይም አስቸኳይ ጉዞ የሚያደርጉ መንገደኞች ሌላ የጉዞ አማራጭ እንዲጠቀሙ ሲል መልዕክት አስተላልፏል።
አየር መንገዱ በአየር ፀባይ ምክንያት የተስተጓጎሉ በረራዎች ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው እንደተመለሱ ለመንገደኞች የሚያሳውቅ መሆኑን አስታውቋል።@seco


