አርሶ አደሮችን እና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የብድር አገልግሎት ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዳስታወቀው ባለ አነስተኛ ይዞታ አርሶ አደሮችን እና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የብድር አገልግሎቶችን ይፋ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ተወካይ እና የኮርፖሬት አገልግሎቶች ኤክስኪውቲቭ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ እንደገለጹት ባንኩ ይፋ ያደረገው የብድር አገልግሎት ለሰብል ምርት፣ ለእንስሳት እርባታ፣  ለእቃ ማከማቻ ደረሰኝ፣ ለወተት እና የወተት ተዋፅኦ ምርት፣ ለአትክልት፣ ፍራፍሬ እና አበባ ልማት እንዲሁም ለግብርና ማሽነሪዎች ወይም መሳሪያዎች ግዥ የሚያገለግል ነው፡፡

ባንኩ ይፋ ያደረገው የግብርና ብድር ቀደም ሲል በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሃብቶች ከሚሰጠው ብድር በተለየ ግለሰብና በቡድን የተደራጁ አርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡@seco

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories