በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ አምራቾች ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚቀርቡትን ምርቶች   ለሀገር ውስጥ ገበያ ሊያቀርቡ ነው

ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኤክስፓርት የጥራት ደረጃ የተዘጋጁ ኢንዱስትሪ ምርቶችን በ’ዘመን ገበያ’ ለሸማቾች ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል

ስምምነቱ የኢንዱስትሪ ፓርክ አምራቾች የኤክስፖርት ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶቻቸውን በስፋትና በቅልጥፍና ተደራሽ እንዲያደርጉ ያስችላል ተብሏል።

 ግብይቱ በዲጂታል የሚከናወንና ሙሉ በሙሉ በመረጃ በተደገፈ (Data-driven) ዘመናዊ የክምችትና የሎጂስቲክስ አስተዳደር የሚመራ እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን የኦፕሬሽን ወጪን እንደሚቀንስ ተነግሯል።

 በዘመን ገበያ   ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ አልባሳት፣ ጨርቃ ጨርቅ እና ጋርመንት፣ የቆዳ ውጤቶች፣ ቦርሳዎች እና የፋሽን መለዋወጫዎች፣ እሴት የተጨመረባቸው የግብርና ምርቶች፣ የቅባት እህሎች፣ ቡና፣ እና የምግብ ምርቶች፣ የሞባይል ስልኮች፣ ታብሌቶች፣ የቤት ውስጥ መገልገያዎች (ቲቪ፣ ፍሪጅ)፣ እና የኤነርጂ ምርቶች፣ የመድሀኒት ምርቶች እና የተለያዩ የህክምና መርጃ መሳሪያዎችእንዲሁም ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የሚውሉ ኬሚካሎች፣ ማዳበሪያ እና የግንባታ ግብአቶች፣ የሴራሚክ እና የእንጨት ውጤቶችን ያካተተ ግብይት መፈጸም እንሚቻል ነው የተገለጸው።ስምምነቱ በዋናነት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን (IPDC) ስር ያሉ አምራቾችን በዘመን ገበያ የዲጂታል ግብይት ሥርዓት ላይ በመመዝገብ ማሳተፍ፣በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚመረቱ የተለያዩ ምርቶችን ዲጂታል ሥርዓትን በመጠቀም ለአገር ውስጥ ገበያ የሚቀርቡበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ከመነሻ ትዕዛዝ እስከ ግብይት ፍጻሜ ያለውን የሎጂስቲክስ፣ የትዕዛዝ አስተዳደር እና የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ፣በኢንዱስትሪ ፓርኮች ሥነ ምህዳር ውስጥ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራን የሚያካትት የትብብር ማዕቀፎች እንዳካተተ ታውቋል፡፡

ዘመን ገበያ የኢትዮ ቴሌኮምን ሰፊ የዲጂታል መሠረተ ልማት፣ የኢንተርኔት እና የስማርት ስልክ ተደራሽነት እንዲሁም የቴሌብር ሥነ-ምህዳርን በመጠቀም የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ የሚያንቀሳቅስ ብሔራዊ የዲጂታል መገበያያ ፕላትፎርም ሲሆን እ.ኤ.አ. ግንቦት 2025 ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ70,000 በላይ ትዕዛዞችን ያስተናገደ፣ ከ460 በላይ ነጋዴዎችን በማቀፍ የኢ-ኮሜርስ ዘርፍ እየሰራ ነው።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories