ዜኒት ባንክ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማረግ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዝናቡ ይርጋ ዜኒት ባንክ ተወካዮች ጋር በኢትዮጵያ በቅርቡ በተከፈተውን የባንክና የፋይናንስ ዘርፍ የኢንቨስትመንት እድሎችን ውይይት አካሄደዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ ኢትዮጵያ ታማኝና ግዙፍ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማትን ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገራት ጋር የሚደረጉ የንግድ ግንኙነቶች መስፋፋት እና ታላላቅ የመሠረተ ልማትና የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች መኖራቸው ለረጅም ጊዜ የፋይናንስ ዘርፍ ኢንቨስትመንትና ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ ምህዳር መፈጠሩን ተናገረዋል።

የዜኒት ባንክ የውጭ ቅርንጫፎችና የዓለም አቀፍ ገበያ መስፋፋት የቡድን ኃላፊ ኦሉካዮዴ አኪንቢኑ ዜኒት ባንክ በኢትዮጵያ በቅርቡ የተደረጉ የዘርፍ ማሻሻያዎች እና በባንክና የፋይናንስ አገልግሎቶች ነፃነት የተፈጠረውን ዕድል በመጠቀም በአገሪቱ የፋይናንስ ገበያ ላይ ኢንቨስትመንት ለማድረግ ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው አስታውቀዋል።

ባንኩ በአሁኑ ጊዜ በዲጂታል እና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረቱ የፋይናንስ መፍትሄዎችን እንዲሁም በመንግስት የሚመሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ በማድረግ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት እድሎችን እየገመገመ መሆኑን ተናግረዋል።

ዜኒት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤቱን በሌጎስ ናይጄሪያ ያደረገ ሲሆን በአፍሪካ ውስጥ ባሉ ቅርንጫፎችና የተወካይ ቢሮዎችን እና ቁልፍ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ማዕከላትን በመጠቀም የሚንቀሳቀስ ሲሆን የኮርፖሬት፣ የችርቻሮ፣ የዲጂታል እና የመሠረተ ልማት የፋይናንስ አገልግሎቶችን እየሰጠ የሚገኝ ግዙፍ የፋይናንስ ተቋም ነው።seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories