የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዳስታወቀው ባለ አነስተኛ ይዞታ አርሶ አደሮችን እና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የብድር አገልግሎቶችን ይፋ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ተወካይ እና የኮርፖሬት አገልግሎቶች ኤክስኪውቲቭ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ እንደገለጹት ባንኩ ይፋ ያደረገው የብድር አገልግሎት ለሰብል ምርት፣ ለእንስሳት እርባታ፣ ለእቃ ማከማቻ ደረሰኝ፣ ለወተት እና የወተት ተዋፅኦ ምርት፣ ለአትክልት፣ ፍራፍሬ እና አበባ ልማት እንዲሁም ለግብርና ማሽነሪዎች ወይም መሳሪያዎች ግዥ የሚያገለግል ነው፡፡
ባንኩ ይፋ ያደረገው የግብርና ብድር ቀደም ሲል በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሃብቶች ከሚሰጠው ብድር በተለየ ግለሰብና በቡድን የተደራጁ አርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡@seco


