የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተከፈለ ካፒታሉ ከፍ እንዲደረግለት ለሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጥያቄ ማቅረቡ ታወቀ። አየር መንገዱ ይህንን ጥያቄ ከሁለት ዓመታት በፊት አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ጥያቄውን በድጋሚ ማቅረቡ ተሰምቷል።
በአየር መንገድ ግሩፕ ቦርድ ፀድቆ የቀረበውን ይህንን የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄ የኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ቦርድ እየተመለከተው መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች አረጋግጠዋል። ምንም እንኳ የተጠየቀው የካፒታል መጠን በዝርዝር ባይገለጽም፣ ጉዳዩ በከፍተኛ አመራሮች በቅርበት እየተመራ እንደሚገኝ የዘገበው ሪፖርተር ነዉ።@seco


