ሳፋሪኮም የታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ለኢትዮ ቴሌኮም ይፋዊ ጥያቄ ማቅረቡ ተሰማ

በኢቢቪ ዘጋቢ

ተጨማሪ የቴሌኮም ኩባንያ በመሆን ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪኮም ከመነሻውም በአገሪቱ የሚሰራበት ታሪፍ እንደማያዋጣው ሲገልፅ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

ሆኖም ፍሬህይወት ታምሩ የሚመሩት ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት አመታት ከፍተኛ የታሪፍ ቅናሽ በማድረግ ለደንበኞቹ ተመጣጣኝ የድምፅ እና ዴታ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።

ትላንት ታህሳስ 15 ቀን ሳፋሪ ኮም ይፋ እንዳደረገው በስራ እና ኢንቨስትመንት ወጪ መናር በዴታ አገልግሎቱ ላይ መጠነኛ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።

ምንጮች እንደሚገልፁት ኩባንያው ኢትዮ ቴሌኮም ጭማሪ እንዲያደርግ በይፋ ጥይቋል።

ይሁን እንጂ በተለይ ከምንዛሪ ለውጥ ጋር ተያይዞ በተለይ በዴታ አገልግሎት  ላይ ወጪ መጨመሩን ባለሞያዎች ቢናገሩም የኢትዮ ቴሌኮም ውሳኔ አለመታወቁን ገልፀዋል።

ትላንት የሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ንድጌዋን አስከትለው ወደ አዲስ አበባ የመጡት የኬንያው ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በሁለቱ የቴሌኮም ኩባንያዎች ዙርያ መወያየታቸውን ገልፀው ነበር።

በውይይታቸው በሁለቱ መንግስታት ድጋፍ ኩባንያዎቹ ስልታዊ ጥምረት ፈጥረው በቀጠናው በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ስምምነት መደረሱን ነው የገለፁት።

በውይይታቸው የኢትዮ ቴሌኮም የበላይ የሆነው ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታየ እንዲሁም የዘርፉ ተቆጣጣሪ የሆነው ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን የበላይ ባልቻ ሬባ ተገኝተው ነበር።©SECO

Related

Ethiopia’s Health Spending Set to Surge 73% by 2030, Driven by Government Investment

-Health-related taxes and the exploration of debt-swaps for health...

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

Popular Categories