መፍትሄው ወደርሶ እየቀረበ ነው
በቤቶ ወይም በቢሮዎ የኤሌትሪክ ማከፋፈያ ላይ የተሰካውን የቻርጀር ብዛት በአይነ ህሊናዎ ይሳሉ።
ትልቅ መፍትሄ አሁን ወደ እርሶ እየቀረበ ነው
የአውሮፓ ኮሚሽን የተንቀሳቃሽ ኤሌክትሮኒክ አምራቾች ማለትም ስልክ፣ ማዳመጫ፣ ታብ፣ ካሜራ፣ ጌሞች፣ ስፒከር እና መሰል መገልገያዎች በተመሳሳይ ቻርጀር (ታይፕ ሲ/ USB-C) እንዲሰሩ ውሳኔ ማሳለፉን ያውቃሉ።
በዚህም ምርታቸውን ለአውሮፓ ህብረት የሚያቀርቡ አምራቾች በተመሳሳይ ቻርጀር የሚሰራ ምርት እንዲያቀርቡ ነው የተገደዱት።
ለዚህም ነው አፕል ስልኮቹ እና ሌሎች መሳሪያዎቹ ላይ የቻርጅ መቀበያ ለውጥበያደረገው።
ውሳኔው ከላብቶፕ በስተቀር ቀነ ገዱ ያለፈ ሲሆን።
በታይፕ ሲ ቻርጅ የሚደረግ ላብቶፕ ላይ ህጉ ሙሉ ለሙሉ በቀጣዩ ሚያዝያ 2018 ዓም የሚተገበር ይሆናል።
የአስገዳጅ ህጉ ጥቅሞች
የኤክትሮኒክስ ብክነት መቀነስ። የተለያዩ ቻርጀሮችን መጠቀም ማቆም በአመት እስከ 1000 ቶን ብክነት ማስቀረት ይቻላል።
ሸማች ለሚገዛው አዳዲስ መሳሪያ ተጨማሪ የቻርጀር ወጪ አይኖርበትም። ገንዘቡን ይቆጥባል።
የምርት አይነት እና ብራንድ ቢለያይይም በተመሳሳይ ቻርጀር መጠቀም ይቻላል።
ምርትን በተሻለ ዋጋ ያለ ቻርጀር መሸጥ ያስችላል።
የኮሚሽኑ ህግ በተጨማሪ ታሳቢ ያደረገው የፈጣን ቻርጅን/ fast charge ቴክኖሎጂ ያለብራንድ ልዩነት እውን ማድረግ ነው።
በነጋራችን ላይ ህጉ ከህብረቱ ውጪ ባሉ ሌሎች ገበያዎችም ላይ ተፅእኖ ፈጥሯል
ሸማች እና መሪ አቅም ሲነረው ይሏል እንዲህ ነው።@seco


