ኢትዮ ቴሌኮም የ23% አማካይ የዋጋ ማስተካከያ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም ለሚድያ አካላት በላከው እና ለደንበኞቹ በተለያዩ ማህበራዊ ገፆቹ ባሰራጨው መግለጫ በአሁኑ ወቅት ያለውን ማክሮ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ፣ የአገልግሎት ጥራትን በዘላቂነት ለማስጠበቅ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብሏል።

እናም የአገልግሎት ጥራትን በዘላቂነት ለማስጠበቅና የቴክኖሎጂ አቅሙን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ የታሪፍ ማስተካከያ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ኢትዮ ቴሌኮም በአማካይ የ23% የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።

ይህ ማስተካከያ የደንበኞችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲቻል ሶስት አበይት ነጥቦችን ማካተቱንም የጠቆመ ሲሆን፡፡ እነዚህም፦

• የቴሌብር ልዩ ስጦታ ማዕቀፍ፦ በቴሌብር በኩል ጥቅል ሲገዛ የነበረው የ10% ቅናሽ ወደ 20% ከፍ እንዲል ተደርጓል።

• ዋጋቸው ያልተቀየሩ ጥቅሎች፦ በርካታ ደንበኞች የሚጠቀሙባቸው 38 የተለያዩ ጥቅሎች ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም።

• ዲጂታል አካታችነትን ለማስቀጠል፦ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቀሙባቸው የ1 ብር፣ የ2 ብር፣ የ5 ብር እና የ1 ሰዓት ጥቅሎች ባሉበት እንዲቀጥሉ ተወስኗል።

ኢትዮ ቴሌኮም የዋጋ  ጭማሪው ለኢትዮጵያውያን የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚነት ቀጣይነት እንዲሁም የሀገሪቱን አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያፋጥን እንዲሆን በማሰብ ተመጣጣኝ  እንዲሆን ማድረጉን ገልፃል፡፡

የቴሌኮም ዘርፉን የወጪ ጫና መብዛትና የዘርፉ ተዋናዮች ዋጋ እንዲጨምር በተደጋጋሚ ያሳደሩትን ጫና ተከትሎ ኢትዮ ቴሌኮም የዋጋ ማሻሻያ ሊያደርግ እንደሚገደድ ቅዳሜ ገበያ መዘገቧ ይታወሳል፡፡@seco

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories