የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ለአልጀዚራ በሰጡት ልዩ ቃለ ምልልስ አሸባሪ ቡድኖች ISIL እና አልሸባብ የሶማሊያን ህዝብ ኑሮ እና ደህንነትን በማውደም ተጠያቂ መሆናቸውን ገልፀው ቡድኖቹ እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና እንድትሰጥ በር ከፍተዋል ሲሉ ነው የከሰሱት።
በሌላበኩል እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን የነጻ አገርነት ዕውቅና በመቃወም እስላማዊው ታጣቂ ቡድን አል ሻብብ ሶማሊያውያን በእስራኤል ላይ ጠመንጃ እንዲያነሱ ጥሪ አቅርቧል። የቡድኑ ቃል አቀባይ ባስተላለፈው በቪዲዮ በተቀረጸ መልዕክት ሶማሊያውያን አገራቸውን ከእስራኤል ለመከላከል ታጥቀው እንዲነሱ ጥሪ አስተላልፏል።@SECO


