የጢስ ዓባይ 1 የኃይል ማመንጫ ጣቢያን ዳግም ወደ ሥራ ለመመለስ የጥገና ሥራዎች መጀመሩ ተሰማ

ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት መስጠት አቁሞ የቆየውን የጢስ ዓባይ 1 የኃይል ማመንጫ ጣቢያን ዳግም ወደ ሥራ ለመመለስ የጥገና ሥራዎች መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

ጣቢያው ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ የቆየው በመለዋወጫ ዕቃዎች እጥረት እና በከፍተኛ የደለል ክምችት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

ተቋሙ እንዳስታወቀው፣ የጢስ ዓባይ 1 ማመንጫ ጣቢያ ከጢስ ዓባይ 2 ጋር የጋራ የውሃ ማስገቢያ በር (Intake gate) የሚጠቀም ቢሆንም፣ የራሱ መከላከያ በር ባለመኖሩ የውሃ ማስተላለፊያ ቱቦው በደለል ተዘግቶ ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት ይህንን ችግር በመቅረፍ ጣቢያውን ወደ አገልግሎት ለማስገባት ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ ተብሏል።

ከ60 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው ይህ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ፣ 11.4 ሜጋ ዋት ኃይል የማምረት አቅም እንዳለውም ተገልጿል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories