የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ 47.6 በመቶ ያህሉ የኢትዮጵያ ስደተኞችና ቤተሰቦቻቸው የአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ (Welfare) ተቀባይ መሆናቸውን ገለጹ።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም 71.9 በመቶዎቹ ትውልደ ሶማሊያውያን በተመሳሳይ በመንግሥት ድጋፍ ውስጥ የታቀፉ መሆናቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን መረጃ ያጋሩት፣ በተለይ በሶማሊያውያን ስደተኞች ላይ ያነጣጠረ ወቀሳ ሲያቀርቡ ከቆዩ በኋላ ነው። ሶማሊያውያንና ትውልደ ሶማሊያውያን በብዛት በሚኖሩባት በሚኒሶታ ግዛት ውስጥ፣ የሕፃናት እንክብካቤን ጨምሮ መንግሥት የሚያቀርበው ነፃ ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚመዘበር ፕሬዝዳንቱ በተደጋጋሚ ሲወነጅሉ መቆየታቸውን ዋዜማ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ግዛቲቱ ውስጥ የመንግሥትን ነፃ ድጋፍ በተጭበረበረ መንገድ የሚጠቀሙ ትውልደ ሶማሊያውያን ዜጎችን ከሀገር እንደሚያባርሩ ጭምር በመዛት ላይ ይገኛሉ። ይህ የፕሬዝዳንቱ መግለጫ በአሜሪካ በሚኖሩ የስደተኛ ማህበረሰቦች ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።@SECO


