በኢቢቪ ዘጋቢ
በቅርቡ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የአገራት ዶላር በመጠባበቂ ገንዘብ የመያዝ ሁኔታ በ20 አመት ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ቅናሽ ታይቶበታል።
እኤአ ከ1990ዎቹ አጋማሽ ወዲህ የዶላር የመጠባበቂያ ገንዘብነት ድርሻ በከፍተኛ መጠን አድጎ የነበረ ሲሆን።
እኤአ በ2000 የዶላር የመጠባበቂያ ድርሻ ከ70 በመቶ በላይ ተሻግሮ ነበር።
አሁን ላይ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት የዶላር የመጠባበቂያ ገንዘብነት ድርሻ በ20 አመታት ውስጥ የ40 በመቶ ቅናሽ ታይቶበታል።
ይሁንና ዶላር አሁንም የአገራት ዋነኛ መጠባበቂ ሆኖ እየመራ ይገኛል። እንደ IMF ያሉ ተቋማት የዶላር የመጠባበቂያ ድርሻ ከ50 በመቶ በላይ እንደሆነ ነው የሚገልፁት።
የዶላር ድርሻ ለምን ቀነሰ
ማእከላዊ ባንኮች ወርቅን እንደ መጠባበቂያ የመጠቀም ዝንባሌያቸው እየጨመረ መምጣት ለዶላር የመጠባበቂያ ግልጋሎት ቅናሽ በምንያት ሊነሳ ይችላል።
እንደሚባለው ወርቅን በመጠባበቂ መጠቀም እኤአ ከ1990ዎቹ መጀመሪያ ወዲህ ከፍተኛ መጠን ላይ ደርሷል።
በዚህም ድርሻው ወደ 28 በመቶ ነው ያሻቀበው።
የወርቅ የመጠባበቂያ ድርሻ ከዪሮ፣ ፓውንድ እና የን ድምራዊ ድርሻ የሚበልጥ ነው።
ተጨማሪ ሀብት ወደ መድረኩ መምጣት ለዶላር መጠባበቂያ ቅናሽ የታከለ ምክንያት ሆኗል።
ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የቢትኮይን ወደ መጠባበቂያ ሜዳው መግባት ተጠቃሽ ነው።
የአለም ለውጥ
ለዶላር መጠባበቂ ግልጋሎት መቀነስ የአሜሪካ ፖለቲካዊ ፍላጎት ገፊ እንደሆነ ነው ባለሞያዎች የሚገልፁት።
የጂኦፖለቲካ ውጥረት፣ ማእቀብ እና ሌሎች ተያያዝ ምክንያቶች አገራት አማራጭ እንዲያስሱ እየገፋቸው እንደሆነ ነው የሚጠቀሰው።
እንደ ቻይና፣ ሩስያ እና ህንድ ያሉ አገራት ከቀደመው በተለየ በራሳቸው ገንዘብ እርስ በርስ ፍላጎታቸው ጨምሯል።
ምንም እንኳ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ብሪክስን እያስጠነቀቁ ቢሆንም አዳጊ የሚባሉት የብሪክስ አገራት የጋር የመገበያያ መንገድ እየፈለጉ መሆኑ ለዶላር ሌላኛው አደጋ እንደሆነ ነው የሚጠቀሰው።
የዶላር መጠባበቂያነት መዳከም አሜሪካ በአለም ንግድ እና የፋይናንስ ስርአት ላይ ያላትን ተፅእኖ የሚያዳክም እንደሚሆን ቢወሳም ዶላርን ካለው ተፅእኖ መስወጣት ግን እጅግ ውስብስብ እንደሆነ ነው የሚገለፀው።
ቁጥሮች!
ቀዳሚ መጠባበቂ ገንዘቦች አማካኝ ድርሻ
1. ዶላር (57%)
2.ዩሮ (20%)
3. የን (5%)
4.ፓውንድ (5%)
5.ዩዋን/አርኤምቢ (2%)


