ደቡብ አፍሪካ ስታርሊንክን በመከልከሏ ኤሎን መስክ ውሳኔው “ዘርን መሠረት ያደረገ ነው” ሲል ወቀሰ

የቢሊየነሩ ኤሎን መስክ የሳተላይት ኢንተርኔት ኩባንያ ስታርሊንክ (Starlink) በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳይሰጥ መከልከሉን ተከትሎ፣ ማስክ ውሳኔው የቆዳ ቀለምን መሠረት ያደረገ ነው ሲል በድጋሚ ወቀሳ ሰነዘረ።

ኩባንያው በደቡብ አፍሪካ 121.8 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግና ለ5,000 የገጠር ትምህርት ቤቶች ነፃ የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት ቃል ቢገባም፣ በአገሪቱ የቴሌኮም ሕግ ምክንያት የሥራ ፈቃድ ተከልክሏል።

ይህ ሕግ ማንኛውም የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪ ተቋም 30 በመቶ የሚሆነው የባለቤትነት ድርሻ ቀደም ሲል በነበረው የዘረኛ ሥርዓት ለተበደሉ (ጥቁር) ደቡብ አፍሪካውያን መሰጠት እንዳለበት ይደነግጋል።

ኤሎን መስክ በበኩሉ ይህንን መስፈርት በቀጥታ የባለቤትነት ድርሻ ከመስጠት ይልቅ፣ ማኅበረሰቡን በሚጠቅሙ ሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮች ማሟላት እንደሚቻል ቢገልጽም ተቀባይነት አላገኘም።

ስታርሊንክ ሕጉን በማክበር ከባለቤትነት ድርሻ ጋር እኩል የሆነ የገንዘብ ኢንቨስትመንት ለሕዝቡ ለማቅረብ ያቀረበው አማራጭ ውድቅ መደረጉንም ማስክ ተችቷል።

መስክ አክሎም መንግሥት መጠነኛ የአሠራር ማሻሻያ ቢያደርግ ስታርሊንክ በሳምንታት ውስጥ መላውን ደቡብ አፍሪካ ማዳረስ እንደሚችል ገልጿል።

ይህ በደቡብ አፍሪካ የታየው ዕገዳ ስታርሊንክ በሌሎች የአፍሪካ አገራት እያደረገ ያለውን መስፋፋት አላገደውም። በአሁኑ ወቅት ኩባንያው በናሚቢያ፣ በካሜሩን፣ በሌሴቶ፣ በሶማሊያ እና በኮንጎ የሥራ ፈቃድ አግኝቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ማስክ አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ባለሃቱ የትውልድ አገሩ በሆነችው ደቡብ አፍሪካ የተጣለበትን ዕገዳ “ኢ-ፍትሐዊ” በማለት መቃወሙን ቀጥሏል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories