የአፄ ኃይለስላሴ የልጅ ልጆች ሆቴላቸውን ሸጡ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን መግዛቱን አስታወቀ

ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አፄ ኃይለስላሴ ልጃቸው ልዑል መኮንን በመኪና አደጋ ምክንያት በድንገት ማረፋቸውን ተከትሎ ለልጅ ልጆቻቸው መተዳደሪያ እንዲሆን የሰሩላቸው መሆኑ ይነገራል።

ዋቢ ሸበሌ ሆቴል በ1957 ዓም ተጀምሮ በ1960 ዓም ተጠናቆ ስራ ቢጀምርም በወታደራዊው መንግስት በ1967 ዓ.ም ተወርሶ በመንግስት ስር ሆኖ አገልግሎት እየሰጠ ቆይቷል፡፡

ኢህአዴግ  አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ በሚሊኒየሙ መባቻ ለቀድሞ ባለቤቶቹ ማለትም ለልዑል መኮንን ልጆች መመለሱ አይዘነጋም።

ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም  የአየር ንብረት  ለውጥ ጉባኤ ለማዘጋጀት መመረጧን ተከትሎ ሚድሮክ  ለተሳታፊዎች  ከሚሰራቸው ሆቴሎች አንዱ ሲሆን ዘመናዊና ቅንጡ በሆነ መልኩ የማሪዮት ደረጃን (autograph collection by Marriot ) ጠብቆ የሚታደስ ይሆናል ተብሏል።

ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና የዋቢ ሸበሌ ሆቴል አክሲዮን ማህበር የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን ተፈራርመዋል።

የሆቴሉ አገልግሎት በዘርፉ አለም በደረሰበት ደረጃ በማዘመን ለእንግዶች ምቹና ጥራቱን የጠበቀ የማረፊያ ቦታ ለማድረግ እንደሚሰራ አቶ ጀማል ተናግረዋል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories