በዓለም ትልቁ ግድብ የማፍረስ ፕሮጀክት፤ ተፈጥሮ ወደ ቀድሞ ይዞታዋ እየተመለሰች ነው

አሜሪካ በዓለም ትልቁ የተባለውን የግድብ ማፍረስ ፕሮጀክት በክላማዝ ወንዝ ላይ ተግባራዊ በማድረግ፣ ለበርካታ አስርት ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የተፈጥሮ ሚዛን የመመለስ ሥራ ጀምራለች።

ይህ ታሪካዊ እርምጃ ለዘመናት የነበሩ ግድቦችን በማንሳት 420 ማይል (675 ኪሎ ሜትር) የሚሸፍን የወንዝ አካልን ለሳልመን (Salmon) ዓሦች መራቢያና መኖሪያነት ክፍት አድርጓል።

የግድቦቹ መነሳት የወንዙን የሙቀት መጠንና ፍሰት ወደ ቀድሞ ሁኔታው እንዲመለስ በማድረግ፣ መላው የስነ-ምህዳር ሥርዓት ራሱን እንደገና እንዲገነባ ዕድል ፈጥሯል።

ቀደም ሲል በግድቦች ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የወንዙ ጉዞ አሁን ላይ ቀጣይነት ያለው የተፈጥሮ መስመሩን መልሷል።

ይህ ቀጣይነት ያለው ፍሰት ደግሞ ተፈጥሮ የምትመራበትን የክብደት ዑደት (circular life) ዳግም እንዲያንሰራራ አድርጓል። ግድቦቹ መነሳት በጀመሩ ማግስት ተፈጥሮ የላከችውን “መንገድ ተከፍቷል” የሚል ምልክት ዓሦቹ በፍጥነት የተረዱት ሲሆን፣ ባለፉት 100 ዓመታት ዝግ የነበሩ የቀዝቃዛ ውሃ ስፍራዎችንና የተፈጥሮ ማራቢያ ቦታዎችን አሁን ላይ ለሳልመን ዓሦች ምቹ ሆነዋል።

ይህ ፕሮጀክት በታሪክ መዝገብ ላይ ብቻ ቀርቶ የነበረውን የተፈጥሮ ሀብት ወደ እውን ዓለም የመለሰ አስደናቂ ክንውን ሆኖ ተመዝግቧል።@SECO

Related

Ethiopia’s Health Spending Set to Surge 73% by 2030, Driven by Government Investment

-Health-related taxes and the exploration of debt-swaps for health...

New ECMA Chief Grants Licences to Two More Investment Banks, Expanding Capital Market Players

The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA), under its newly...

Top 10 Largest Cities in Sub-Saharan Africa by 2050: World Bank Population Forecast

The World Bank projects major population growth in Sub-Saharan...

Popular Categories