ነዳጅን በባቡር ለማጓጓዝ የሚያስችል የሙከራ ፕሮጀክት ዛሬ ይጀመራል ተባለ

ኢትዮጵያ ስልታዊ የሆኑ ምርቶችን የምታጓጉዝበትን መንገድ ለማዘመን በወሰደችው እርምጃ፣ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ከብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያ (ኖክ) ጋር በመተባበር ነዳጅን በባቡር ለማጓጓዝ የሚያስችል የሙከራ ፕሮጀክት ዛሬ ማክሰኞ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ይጀምራሉ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትዕዛዝ የተጀመረው ይህ ተነሳሽነት ለዓመታት ሳይሠሩ የቆዩ 110 የነዳጅ ማጓጓዣ ዋጎኖችን ወደ ሥራ የሚያስገባ ሲሆን፣ ዛሬ ከአዲስ አበባ የንዶዴ የባቡር ዴፖ የሚጀመረው የመጀመሪያው የሙከራ ጉዞ 120,000 ሊትር ናፍጣን ወደ መሀል ሀገር ያጓጉዛል።

ይህንን ስራ ውጤታማ ለማድረግ በጅቡቲ ሆራይዘን ተርሚናል እና በአቅራቢያው በሚገኘው የባቡር ጣቢያ መካከል የ1.5 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ትስስር ለመፍጠር ከጅቡቲ ወገን ጋር ድርድር እየተደረገ ይገኛል።

ነዳጅ እና ማዳበሪያን በመሰሉ ስልታዊ ምርቶች ላይ የባቡር ትራንስፖርትን መጠቀም የሀገሪቱን የሎጂስቲክስ ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ለማዳበሪያ ትራንስፖርት ብቻ የሚባክነውን እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ወጪ ለማዳን ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል።

የሙከራው ሂደት አስፈላጊውን የደህንነት እና የጥራት መስፈርቶች ካሟላ በኋላ መጠነ-ሰፊ የነዳጅ ትራንስፖርት በይፋ የሚጀመር ሲሆን፣ ይህም የሎጂስቲክስ ሰንሰለቱን ከማቀላጠፉ ባለፈ በሀገሪቱ የሚታየውን የነዳጅ እና የማዳበሪያ ገበያ ለማረጋጋት ትልቅ ሚና ይጫወታሉ ሲል የዘገበው ካፒታል ነዉ።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories