የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የስድስት ወራት ስራ አፈጻጸም በገመገመበት መድረክ ላይ እንደተገለጸው ባለፈው በጀት ዓመት ዓመቱን ሙሉ ከሰራዉ አረቦን በግማሽ ቢሊየን የበለጠ አረቦን በ6 ወራት መስራት መቻሉ ተነግሯል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት 13 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ እንዳገኘ ነው የተገለጸው፡፡
የተገኘው ገቢም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት 48 በመቶ እድገት ከማሳየቱም በተጨማሪ በጠቅላላ የመድን ዘርፍ የገበያ ድርሻውም 45 ነጥብ 7 በመቶ ደርሷል፡፡
ድርጅቱ በባለፈው ሙሉ በጀት ዓመት በጥቅሉ ከሰበሰበው አረቦን በግማሽ ቢሊየን የላቀ አረቦን በስድስት ወር ብቻ መሰብሰብ እንደቻለ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አቤል ታደሰ ተናግረዋል፡፡@SECO


