የአፍሪካ መንግሥታት በፈረንጆቹ 2026 የሚጠበቅባቸው የውጭ ምንዛሬ ዕዳ ክፍያ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ፣ በሀገራቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችትና በኢኮኖሚ መረጋጋት ላይ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ኤስ ኤንድ ፒ ግሎባል ሬቲንግስ አስጠነቀቀ።
ተቋሙ ባወጣው የአፍሪካ ሉዓላዊ ሀገራት ትንበያ፣ የመንግሥታት የውጭ ዕዳ ክፍያ እ.ኤ.አ ከ2012 ጋር ሲነጻጸር በሦስት እጥፍ ማደጉን አመልክቷል። እንደ ሪፖርቱ ግምት ከሆነ፣ ዘንድሮ የአፍሪካ ሀገራት በአጠቃላይ ከ90 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ዕዳ ክፍያ ይጠበቅባቸዋል።
ከዚህ ግዙፍ የዕዳ ክፍያ ውስጥ ሲሶውን (27 ቢሊዮን ዶላር ገደማ) የምትሸፍነው ግብፅ ስትሆን፣ አንጎላ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ናይጄሪያም ከፍተኛ ክፍያ የሚጠበቅባቸው ሀገራት ተርታ ተሰልፈዋል።
ምንም እንኳን በአህጉሪቱ የሚታየው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፍላጎትና የብድር ደረጃ መሻሻል ተስፋ ሰጪ ቢሆንም፣ የዕዳው መጠን ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት አንጻር በአማካይ በ61 በመቶ ከፍ ብሎ እንደሚቀጥልና ይህም ሀገራቱ አማራጭ የፋይናንስ ምንጮችን እንዲፈልጉ ጫና እንደሚፈጥርባቸው ተመልክቷል።SECO


