ግብፅ በአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ላይ እንደምትሳተፍ አስታወቀች

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ሀገራቸው በአፍሪካ ሕብረት አዲሱ የሶማሊያ የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ ላይ እንደምትሳተፍ በይፋ ማረጋገጣቸውን ተከትሎ፣ በካይሮ እና በሞቃዲሾ መካከል ያለው ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል።

ፕሬዝዳንቱ ከሶማሊያው አቻቸው ሐሰን ሼክ መሐሙድ ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ እንደገለጹት፣ ይህ ውሳኔ ግብፅ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት፣ አንድነትና ደኅንነት ያላትን ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነው።

 አል-ሲሲ ግብፅ የሶማሊያን ግዛታዊ አንድነት የሚጋፋ ማንኛውንም እርምጃ በጽኑ እንደምትቃወም በመግለጽ፣ የግብፅ ጦር መሳተፍ በቀጠናው በተለይም በአፍሪካ ቀንድና በቀይ ባሕር አካባቢ ያለውን መረጋጋት ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አጽንኦት ሰጥተዋል።

በበኩላቸው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ፣ ግብፅ ለሶማሊያ እያደረገች ላለው ወንድማማቻዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ይህ ትብብር የሁለቱን ሀገራት የጋራ ብሔራዊ ጥቅምና የቀጠናውን ደኅንነት ለማስጠበቅ የሚኖረው ሚና የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories