የብሔራዊ ባንክ ገዢዉ እዮብ ተክለኝ ለአፍሪካ ሀገራት የቀጠናዊ የፋይናንስ ተቋም እንዲቋቋም ጥሪ አቀረቡ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  የአፍሪካ ሀገራት የራሳቸውን አህጉራዊ የፋይናንስ ድጋፍ ሥርዓት ሊዘረጉ እንደሚገባ አሳሰበ።

በሳዑዲ አረቢያ እየተካሄደ በሚገኘው “የአሉላ አዳጊ ኢኮኖሚዎች ጉባኤ” ላይ የተሳተፉት የባንኩ ገዢ እዮብ ተካልኝ ፤ የአፍሪካ ሀገራት በአሁኑ ወቅት ካለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ የደህንነት መረብ ተጠቃሚ የመሆናቸው ዕድል እጅግ ውስን መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት ብዙዎቹ ሀገራት በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ ክምችት እና በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ድጋፍ ላይ ብቻ እንዲወሰኑ መገደዳቸውን ጠቁመዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ የአፍሪካን ነባራዊ ሁኔታና ተጋላጭነት ያገናዘበ፣ በተመሳሳይ ጊዜም ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ሥርዓት ጋር የተሳሰረ የቀጠናዊ ፋይናንስ ስምምነት መመስረት ለኢኮኖሚ ጥንካሬ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።@SECO

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories