ከ940 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነቡ  የፀሃይ ኃይል ፕሮጀክቶች ተመረቁ

ቅዳሜ ገበያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘችው መረጃ እንደሚያሳየው በሶማሌ ክልል ከ940 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነቡ አራት የፀሃይ ኃይል ፕሮጀክቶች ተመረቀው 24 ሰዓት አገልግሎት መሥጠት ጀምረዋል፡፡

በዲግ፣ በኑስደሪቅ፣ በጋሻሞ እና በምርቃን የተገነቡት እነዚህ የጸሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች፤ የጤና እና የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ከ9 ሺ 500 በላይ ደንበኞችን የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው፡፡

አራቱ ፕሮጀክቶች በድምሩ 1 ነጥብ 8 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፤ ለፕሮጀክቶቹ ግንባታ 20 ነጥብ 42 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ፣ 78 ነጥብ 46  ኪ.ሜ  ዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 21 የተለያዩ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች ተተክለዋል፡፡

ከ940 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ወጥቶባቸው የተገነቡት እነዚህ ፕሮጀክቶች፤ ሙሉ ወጪው የተሸፈነው ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ብድር ነው፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ 38 የጸሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኝ  ሲሆን ከዚህም ውስጥ በሶማሌ ክልል  8 የፀሀይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች  አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories