ሁለት ገለልተኛ ባለሞያዎች በገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ውስጥ ተካተቱ

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ፣ የኢቢቪ ዘጋቢ

ባሳለፍነው አመት በተሻሻለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የማቋቋሚያ አዋጅ አንቀፅ 23 መሰረት ማእከላዊ ባንኩ የገንዘብ ፖሊሲ ላይ ለቦርድ የውሳኔ ሃሳብ አዘጋጅቶ የሚያቀርብ ኮሚቴ እንዲያቋቁም ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በአዋጁ መሰረት ይህ ኮሚቴ ከታህሳስ 2017 ዓም አንስቶ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ገዥው ሰብሳቢ ምክትል ገዥ ደግሞ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑበት ሰባት አባላት አሉት፡፡

ሆኖም በአዋጁ አንቀጽ 23 ንኡስ አንቀጽ 3 መሰረት ባንኩ የዕከላዊ ባንኩ ሰራተኛ ያልሆኑ ሁለት ገለልተኛ አባላት ማካተት እንደሚችል በሚጠቅሰው መሰረት ለዘርፉ የተገባ የሞያ እና እውቀት ያላቸውን ሁለት ገለልተኛ አባላት ማካተቱን ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡

ብሄራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው መረጃ የተመረጡት ሁለት ገለልተኛ አባላት ሹመት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመራው የብሄራዊ ባንክ ቦርድ ይሁንታ አግኝቷል፡፡

በዚህም መሰረት ቀደም ብለው ተካተው ከነበሩ የኮሚቴ አባላት የሚቀነሱ ይኖራሉ፡፡

የሁለቱ አዳዲስ አባላት መምጣት የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴውን ትንተና አቅም ያሳድጋል የተባለ ሲሆን፤ የቦርድ ውሳኔም በመረጃ እና ማስረጃ የተደገፈ እንዲሆን ያስችላል ነው ያለው ማእከላዊ ባንኩ፡፡

ብሄራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ አዳዲስ የተመረጡት የፖሊሲ ኮሚቴ አባላት የካበተ ልምድ ያላቸው የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎች፣ ሰፊ የትምህርት መሰረት እና በፖሊሲ እና ማክሮኢኮኖሚክ ትንተና የዳበረ ልምድ ያካበቱ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ይሁንና ስለተመረጡት ግለሰቦች ማንነት ይፋ አላደረገም፡፡

ቀደም ባለው ዘመን ማእከላዊ ባንኩ ከ 9 በላይ ባለሞያዎች ያሉት የገንዘብ ፖለሲ ኮሚቴ አባላት ይዞ ለውስጥ ትንተና ይሰራ እንደነበር መረጃዎ ያሳያሉ፡፡ ሆኖም የኮሚቴው ምስረታ በአዋጅ የተካተተው አምና በተከለሰው ህግ ነው፡፡

የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ከተቋቋመበት ካለፈ አመት አጋማሽ አንስቶ 5 ስብሰባዎች አድርጎ በገንዘብ ፖሊሲ ላይ የተለያዩ ምክረ ሃሳቦችን በማጠናቀር ለቦርድ የውሳኔ ሃሳብ በማሰጠት የተረጋጋ ኢኮኖሚ እንዲፈጠር በተለይ የዋጋ ግሽበትን በተቀናጀ እና በመረጃ እና እውቀት ላይ በተመረኮዘ መልኩ ለመቆጣጠር የበኩሉን ሚና እንደተጫወተ ይገለጻል፡፡

የብሄራዊ ባንክ አዋጅ በ2000 ዓ.ም ተሻሽሎ የነበረውን ህግ በርካታ ክፍሎች የቀየረ ሲሆን በተለይ መንግስት ከብሄራዊ ባንክ የሚወስደው ቀጥታ ብድር ላይ ልጓም እንዲበጅ እና ግልጽ አካሄድ ኢንዲኖር በማድረግ ከሚሊኒየም በፊት የነበረው አሰራር ተመልሶ እንዲመጣ ያደረገ መሆኑ ጎልቶ ይጠቀሳል፡፡©SECO

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories