-የባንኮች ፍላጎትም ቀንሷል
በኢቢቪ ዘጋቢ
ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛው በተጨማሪ ዛሬ ባከናወነው የውጪ ምንዛሪ ጨረታ 500 ሚሊዮን ዶላር ለመሸጥ ቢያቀርብም የባንኮች ፍላጎት ዝቅተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
የባንኮች የውጭ ፍላጎት መቀነስ ሁኔታ የምንዛሬ ዋጋ በገበያ ይወሰን የሚለው አሰራር በሀምሌ 2016 ዓም ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ብሄራዊ ባንክ ገበያውን ለማርካት ብሎ በሚያደርገው ጨረታ ታይቶ የማይታወቅ መሆኑን ነው ባለሞያዎች የገለጹት፡፡
በእለቱ በተጨማሪነት ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የምንዛሬ የመግዣው አማካኝ ዋጋ ማክሰኞ የካቲት 10 ተደርጎ በነበረው መደበኛ ልዩ የምንዛሬ ጨረታ ተመዝግቦ ከነበረው አንፃር የመግዣ መጠን ቀንሷል፡፡ ወይም የብር የመግዛት አቅም መጠነኛ ጥንካሬ ማስመዝገብ ችሏል፡፡
በዛሬው ጨረታ አንድ ዶላር 153.25 ብር በአማካኝ የተሸጠ ሲሆን፡፡ ማክሰኞ በነበረው ጨረታ አማካኝ አሸናፊ ዋጋ 155.12 ብር ነበር፡፡
በመሆኑም በዛሬው ጨረታ ብር የ 1.2 በመቶ ጥንካሬ ማስመዝገብ ችሏል፡፡
ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 14 በተደረገው ጨረታ 30 ባንኮች ተሳትፈው ሁሉም የወሰዱ ቢሆንም፡፡ ለመግዛት ፍላጎት ያሳዩት ግን ከቀረበው 44.7 ሚሊየን ዶላር ዝቅ ያለ ነው፡፡
በእለቱ ብሄራዊ ባንክ ለመሸጥ ያቀረበው ግማሽ ብሊየን ዶላር ቢሆንም ባንኮች ለመግዛት የጠየቁት ግን 455.29 ሚሊየን ዶላሩን ነው፡፡
በመሆኑም ቀሪው የውጭ ምንዛሬ ሳይሸጥ ቀርቷል፡፡

