ፓርቲው የቀድሞውን መሪውን ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና ምክትላቸውን በክብር ሸኝቷል
አቶ ኢዮብ መሳፍንት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) መሪ የነበሩትን ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በመተካት የፓርቲው መሪ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ፓርቲውን ላለፉት ሰባት ዓመታት ሲመሩ የነበሩትን ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሰናብቶ እዮብ መሳፍንትን የፓርቲው መሪ አድርጎ መርጧል።
ጠቅላላ ጉባዔውን በአድዋ መታሰቢያ አዳራሽ ያደረገው ኢዜማ ከብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተጨማሪ የፓርቲው ምክትል መሪ የነበሩትን አርክቴክት ዮሐንስ መኮንንም በተመሳሳይ አሰናብቷል። በምትካቸውም አቶ ንጋቱ ወልዴ ተመርጠዋል፡፡
ፓርቲው ከመሪዎች ምርጫ በተጨማሪ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶውን ያስተዋወቀ ሲሆን በቀጣይ የሚመራበትን 50 ፖሊሲዎችንም ለአባላቱ ይፋ አድርጓል፡፡@SECO


