የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከAerCap ሁለት ግዙፍ የጭነት አውሮፕላኖችን በኪራይ ሊረከብ ተስማማ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም ከሆነው የአውሮፕላን አከራይ ኩባንያ AerCap ጋር በፈረመው ስምምነት፣ ሁለት የቦይንግ 777-300ER ተሳፋሪ አውሮፕላን የነበሩና ወደ ጭነት አገልግሎት የተቀየሩ (777-300ERSF) አውሮፕላኖችን በኪራይ ለማግኘት መወሰኑን አስታውቋል።

እነዚህ አውሮፕላኖች በፈረንጆቹ 2028 ሁለተኛ ሩብ ዓመት ላይ ለአየር መንገዱ የሚረከቡ ሲሆን፣ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም አቀፍ የጭነት ትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ተወዳዳሪነትና የመሪነት ሚና ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ተገልጿል።

አውሮፕላኖቹን ወደ ጭነት አገልግሎት የመቀየር ሥራውን ያከናወነው የእስራኤል ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪስ (IAI) ሲሆን፣ ሞዴሉም ባለፈው ዓመት በአሜሪካና በእስራኤል የበረራ ፈቃድ ማግኘቱ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት፣ እነዚህ አውሮፕላኖች የአየር መንገዱን የጭነት አቅምና የአሰራር ብቃት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድጉ ናቸው። አክለውም አውሮፕላኖቹ በክልሉ ያለውን የንግድ ልውውጥ በማሳለጥ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የAerCap ዋና ሥራ አስፈፃሚ አይንገስ ኬሊ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን ዘመናዊ አውሮፕላን በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጠቀም ታሪክ እንደሚሰራ ጠቁመው፣ አውሮፕላኖቹ ለአየር መንገዱ ከፍተኛ የወጪ ቆጣቢነትና ውጤታማነትን እንደሚያስገኙ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት በርካታ የቦይንግ 777F የጭነት አውሮፕላኖችን እየተጠቀመ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህ አዲስ ስምምነትም አየር መንገዱ የጭነት አውታሩን ለማስፋፋት የያዘውን ስትራቴጂካዊ ግብ ለማሳካት ትልቅ እምርታ ተደርጎ ተወስዷል።. SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories