በአለምሰገድ እስጢፋኖስ
4ኛው “ኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ 2026 ፎረም ኢትዮጵያ ለቢዝነስ ዝግጁ ናት በሚል መሪ ሀሳብ መካሄድ ጀምሯል
የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) እንደገለጹት ኢትዮጵያ እየሰራች ባለችው ሪፎርም የኢንቨስትመንት ስምምነቶች ወደ ትግበራ የሚገቡበት ፍጥነት ከፍ እያለ ነው።
በኢኮኖሚ ሪፎርሙ ህጎች እና የትግበራ ፍጥነትን እየተሻሻለ መሆኑን ጠቁመው በዚህም ኢንቨስተሮች ኢንቨስት ማድረግ የሚችሉበት ከባቢ እየጨመረ ነው ብለዋል።

ኢንቨስተሮች በተለያዩ ዘርፎች እንዲሰማሩ ኢ ሰርቪስ በተለያየ ደረጃ እየተሰጠ እንደሚገኝ አስረድተው ከአስተዳደር ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።
በሀገሪቱ ሰፊ አምራች ወጣት፣ በመልክዓ ምድር ምቹ የገበያ አማራጮች፣ ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንት ዕድሎች እንዳሉም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ያላትን ሰፊ እምቅ አቅም በመጠቀም በዘርፉ ቀዳሚ ሀገራት ተርታ መሰለፍ እንደምትችል ተጠቆመ
የግል ዘርፍ ልማትን ለማፋጠን በተለይ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ማጠናከር፣ የፋይናንስ ዘርፍን ማዘመን እና አጠቃላይ የኢንቨስትመንት አካባቢን ማሻሻል በኢኮኖሚ እድገት ላይ ዋና ሚና እንዳለው ተነስቷል፡፡
በመንግስት በዓለም አቀፍ ተቋማት እና በግል ዘርፍ መካከል የተጠናከረ ትብብር ለተስፋፋ እድገት እና አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዕድሎች መከፈት አለበት ተብሏል፡፡@SECO


