በኢቢቪ ዘጋቢ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወለድ ነፃ ዘርፍ ሲቢኢ ኑር ሃላፊ ስልጣንን ያላግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ፡፡
የባንኩ ምክትል ፕሬዝደንት እና የሲቢኢ ኑር የበላይ የሆኑት አቶ ኑሪ ሁሴን እና ጸሃፊያቸው አስቴር አያሌው በቁጥጥር ስር የዋሉት ከ3 ሳምንት በፊት መሆኑ ነው የታወቀው፡፡
ሁለቱ ግለሰቦች ሃላፊነታቸውን ላልተገባ ጥቅም በመገልገል እንዲሁም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መያዛቸው ነው የታወቀው፡፡
በፖሊስ አቤቱታ መሰረት የወለድ ነጻ ባንኩ ሃላፊ በስራ አጋጣሚ እጃቸው የሚገባ የተቋም መረጃን ላልተገባ የህገወጥ ጥቅም መገልገያ አድርገዋል ሲል ጥርጣሬውን ለፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡
በተጨማሪ ግለሰቦቹ ደንበኞች ብድር እንዲለቀቅላቸው ጉቦ ይቀበላሉ ሲል ነው የከሰሰው፡፡
ጸሃፊያቸው በበኩላቸው ለሃላፊው ህገወጥ ስራ ተባባሪ በመሆን እና ደንበኞችን በማገናኘት የበኩሏን ስትጫወት ነበር የሚል አቤቱታ ነው የቀረበባቸው፡፡
በመርማሪ መረጃ መሰረት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በባንኩ ወደ ሌላ ቦታ ለመመደብ ተሞክሮ እንደነበር ገልጾ ሁለቱም ምደባውን አለመቀበላቸው ነው የተገለጸው፡፡ ይህም ባሉበት ቦታ የሚያገኙት ህገወጥ ጥቅም ሊቀርባቸው ስለሚችል ምደባውን እንዳልተቀበሉ ሊያስጠረጥረር እንደሚችል ነው በመርማሪው የተብራራው፡፡ በተለይ አስቴር ከነበሩበት ወደ ተሻለ ሃላፊነት እንዲዛወሩ ተመድበው እንቢ ማለታቸው ተጨምሮ ተገለወጿል፡፡
መርማሪዎች ለፍርድ ቤት እንዳስረዱት ምርመራው የተጀመረው ከአጠራጣሪ አስራሮች ጋር በተያያዘ ጥቆማዎች እንዲሁም በመምጣጣቸው በተለይ በአቶ ኑሪ ላይ ተጨማሪ የሙስና መረጃዎች ወደ ህግ አስከባሪ በመድረሳቸው ነው ብለዋል፡፡
ባለፈው ሰኞ ተጠርጣሪዎች ፍርድ የቀረቡ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች ከዋስትና መብት ጋር በተያያዘ ጉዳያቸው በይግባኝ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ እየታየ መሆኑን ፎርቹን ዘግቧል፡፡©SECO

