የኢትዮጵያ እና የቻይና የዕዳ ሽግሽግ ድርድር ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ መሸጋገሩ ተነገረ

በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተመራና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ  ተካልኝ(ዶ/ር) ጨምሮ የገንዘብ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በቻይና እያደረገ የሚገኘውን ስትራቴጂካዊ የፋይናንስ ተልዕኮ ጀምሯል።

​የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት በዋናነት ቀደም ሲል ሲካሄዱ የቆዩ የዕዳ ሽግሽግ ድርድሮችን ማጠናቀቅ እና ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የሚውል የፋይናንስ ስምምነት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

​ልዑካን ቡድኑ በቆይታው ከቻይና ኤክስፖርት-ኢምፖርት (Exim) ባንክ፣ ከኢንዱስትሪያል ኤንድ ኮሜርሻል ባንክ ኦፍ ቻይና (ICBC) እና ከቻይና ልማት ባንክ (CDB) ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርጓል።

ውይይቶቹ የዕዳ አያያዝ ሂደቱን በማጠቃለል እና የኢትዮጵያን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንቶች ለመደገፍ አዲስ ፋይናንስ በማሰባሰብ ላይ ያተኮሩ ናቸው።

​ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በዕዳ ሽግሽግ ድርድሩ ላይ ከፍተኛ መሻሻል መታየቱን ገልጸው፣ ወገኖቹ ሂደቱን ወደሚያጠናቅቁበት የመጨረሻ ምዕራፍ መሸጋገራቸውን አስታውቀዋል። የሂደቱ ስኬታማ መጠናቀቅ መንግሥት ሰፋ ያሉ የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን እና በዕድገት ላይ ያተኮሩ የልማት ተነሳሽነቶችን ለማፋጠን የሚያስችል ምቹ የፋይናንስ ሁኔታ እንደሚፈጥርም አክለዋል።

​በተጨማሪም ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ እና የቻይና ስትራጂካዊ አጋርነት ያለውን ጥንካሬ በማንሳት፣ የፋይናንስ ተቋማቱ ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የሚውለውን የፋይናንስ ጥያቄ ግምገማና ማጽደቅ ሂደት እንዲያፋጥኑ አሳስበዋል።

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያን የቀጣናው የአቪዬሽን ማዕከል ለማድረግና የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ሽግግርን ለመደገፍ ያለውን ከፍተኛ ፋይዳም አስገንዝበዋል፡፡@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories