ዛሬ ጅቡቲ ምርጫ ላይ ነች

 በሙሉቀን የወንድወሰን

ያው አፍሪካ ነው ፕሬዝደንቱ ተወዳድረዋል፡፡ ያሸንፋሉ!

በ1947 በወቅቱ እጅግ ጥቂት ከነበሩ የተማሩ የኢሳ ሱማሌ ቤተሰብ ነው የተወለዱት፡፡

ያራዳ ልጅ ናቸው፡፡ ያውም የድሬዳዋ።

ለድስት አመት እዛው ነው የተማሩት።

በአልያንስ ፍራንሴስ ት/ቤት። ጅቡቲ ከመጡ ወዲህ መድረሳ ገብተው በሃይማኖት ትምህርት ገፍተዋል።

በፖሊስ ኢንስፔክተርነት በፈረንሳይ ሶማሌላንድ የፈረንሳይ ቅኝ ገዥዎችን አገልግለዋል።

ሱማልኛ፣ አማርኛ፣ አረብ፣ ፈረንሳይ እና እንግሊዘኛ ይናገራሉ፡፡ ጣሊያንኛም ይሞክራሉ፡፡

በ1977 ሌላው የድሬዳዋ ተወላጅ አጎታቸው ሀሰን ጉሌይድ ኦፕቲዶ ጅቡቲን ነጻ አገር አሰኝተው ሲነግሱ በ29 አመት እድሜያቸው የአዲሲቷን አገር መንግስት ስልጣን ለማርጋት ቁልፉን የቤተ መንግስት ሃላፊነትን ቦታ ይዘው ሰርተዋል፡፡

የፕሬዝደንት ጽ/ ቤት ሹም በመሆን  ከመሪው ቀጥሎ ትልቅ የሚባለውን ቦታ አዘውበታል፡፡

በዛ ላይ ቁልፉን የደህንነት ስራ ደርበዋል።

ለቀጠናው እጅግ ግምት የሚያሰጠውን እና እውቀት የሚካበትበትን መስክ መርተዋል።

የአገሪቱ የስለላ ቢሮ የበላይ ነበሩ ኢስማኤል ኦማር  ጌሌ።

የሚጠሏቸውም የሚደግፏቸው IOG ይሏቸዋል። ባጭሩ።

በ1999 የአጎታቸውን ህልፈተ ህይወት ተከተወሎ የመሪነት ቦታውን በ51 አመታቸው ተቆናጡ።

ጌሌህ የ78 አመት እንድሜያቸው ላይ ደርሰዋል፡፡

ምንም እንኳን በድሜ ኢሳያስ አፈወርቂ ቢበልጧቸውም፡፡

የዘለቀ የመንግስት ስልጣን በመያዝ የበለጠ እውቀት እና ብስለት በማካበት ለቀጠናው ቀዳሚ ናቸው፡፡

የሚያቋቸው እጅግ ተግባቢ፣ በሳል ዲፕሎማት እና ስልታዊ ብልሃት መገለጫቸው እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡

በተለይ ከነጻነት ወዲህ በሚናጠው የአፍሪካ ቀንድ በብስለት እና ብሩህ አረዳድ የአጎታቸው መንግስት በገለልተኝነት መጓዝ እንዲችል ያገዙ እንደሆኑ ይገለጻል፡፡

በአገሪቱ ተቀናቃኞችን ወደ ራሳቸው በመሳብ እና መፍትሄ በማበጀት የተዋጣላቸው ናቸው፡፡

ይህ አካሄዳቸው ለአገራቸው የተሸለ የፖለቲካ ሰላም አስገኝተዋል በሚል የሚወደሱበት ነው፡፡

ሰላሙ ብዙ የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብም ጠቅሟል ይላሉ ዘርፉን የሚከታተሉ።

አቅመ ቢስ ተደርጋ ትቆጠር የነበረችውን ባለ አንድ ሚሊየን ህዝቧን ጅቡቲ አይዳሰስ አቅም/ሶፍት ፓወር በማጎልበት በተለይ ባለፉት 30 አመታት የተጫወቱት ሚና እጅግ የሚደነቅላቸው ነው፡፡

ባልተረጋጋው የምስራቅ አፍሪካ እና የኤደን ባህረ ሰላጤ የባብል መንደብ መግቢያ በሆነችው አገራቸው እንደ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ ጃፓን እና ቻይና ያሉ ሃያላንን ጭምር በማፍዘዝ ተቀናቃኝ አገራት በጥቂት ኪሎ ሜትር ርቀት የጦር ሰፈር እንዲመሰርቱ ማድረግ የቻሉ ናቸው፡፡

ሰውየው በቀጠናው የዲፕሎማሲ አካሄድ እጅግ የተካኑ እንደሆኑ ይጠቀሳል፡፡

ወደብ ከሩቅ ለመጣ እየፈቀዱ ለጎረቤት ለዛውም ለኢትዮጵያ ለመስጠት ሲያቅማሙ ታይተዋል፡፡

በየመን ግጭት ገለልተኛ ሆነው መቀጠል ብቻ አይደለም ባገራቸው የሚገኘው የአሜሪካ እና አጋሮቿ የጦር ሰፈር የጥቃት ኢላማ እንዳይሆን የሳቸው ሚና ከፍ ያለ እንደነበር ይገለጻል፡፡

የመንግስትን ገንዘብ እንደ ራሳቸው ያዙበታል ቢባሉም ላገራቸው እድገት እና ለውጥ የቀየሱት ስትራቴጂ ከፍተኛ ውጤት አስገኝቶላቸዋል፡፡

የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት የፈጠረው እድል ተጨምሮበት በሳቸው የስልጣን ዘመን የጅቡቲ አመታዊ ጥቅል ምርት በ10 እጥፍ አድጎ ወደ 4.3 ቢሊየን ዶላር እንዲጠጋ አስችለዋል፡፡

ባካባቢው አዛውንት እና በሳል መሪ ናቸው፡፡

ሃያላን እና ሃብታሞቹ የአረብ መንግስታት በቀጠናው ጉዳይ በዋናነት እሳቸውን እንደሚያማክሩ የሚያውቁ ይመሰክራሉ፡፡

ተሰሚ ናቸው፤ ፈታ ያሉ፤ ቀልደኛ!

ሙዚቃ ይወዳሉ አሉኝ፤ በተለይ የጥላሁን እና ማህሙድ ነፍሳቸው ነው ከኢትዮጵያ!

በስልጣናቸው ግን ቀልድ የለም፡፡ ሁለቴ ህገ መንግስት ቀይረዋል በስልጣን ለመክረም፡፡

ዛሬ ከይስሙላ ተፎካካሪ ጋር ለስድስተኛ ጊዜ ተወዳድረዋል እስከ 83 አመት እድሜያቸው በስልጣን ለመዝለቅ፡፡@SECO

Related

Ethiopia’s Health Spending Set to Surge 73% by 2030, Driven by Government Investment

-Health-related taxes and the exploration of debt-swaps for health...

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

New ECMA Chief Grants Licences to Two More Investment Banks, Expanding Capital Market Players

The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA), under its newly...

እስራኤል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አገሯ እንዳይገባ አገደች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን በበረራ ሰራተኛው ምክንያት ወደ...

Popular Categories