ዩጋንዳ ጥሬ ቡናን ወደ ውጭ መላክን በመግታት እሴት በመጨመር የምታገኘውን የኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማሳደግ ማቀዷ ነው የተገለፀው።
ጥሬ ቡናን ወደ ውጭ መላክ ስራን እና ሀብትን አሳልፎ መስጠት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ተቀነባብሮ ለገበያ በማቅረብ ከፍተኛ ገቢ ማግኘት ያስችላል ተብሏል።
ከዚህም በተጨማሪ ቡናው በሀገር ውስጥ መዘጋጀቱ በማሸግ፣ በማከማቸት እና በሎጂስቲክስ ዘርፎች ሰፊ የስራ እድል እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።
ዩጋንዳ በቅርቡ ኢትዮጵያን በመቅደም በአፍሪካ ከፍተኛውን የቡና መጠን ወደ ውጭ በመላክ ቀዳሚ መሆኗ መዘገቡ ይታወሳል።@SECO


