የዳሸን ባንክ 30 ዓመታትን ጉዞ የሚዘክር ዳሸን ኤክስፖ ተከፈተ

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ

ኤክስፖው ለዘጠኝ ቀናት በዋናው መሥሪያ ቤት እንደሚቆይ ተጠቁሟል።

በዳሸን ኤክስፖ ባንኩ ከደንበኞች የአገልግሎት ተሞክሮና ባህል ጋር በማዛመድ የተገበራቸውን አሰራሮች፣ ከቁልፍ አጋር ተቋማት ጋር ያለውን መስተጋብር ‘ ባንኩ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ በተለይም ከዲጂታል አገልግሎት ስርፀት ቀዳሚነት ጋር በተገናኘ ያክናወናቸውን አበርክቶዎች ይተዋወቃሉ ተብሏል።

ዳሸን ባንክ ሴቶችን በሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ የማብቃት መርህን በመከተል እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን፤ ስምንተኛ ዓመቱን ያስቆጠረው የዳሽን ባንክ የወለድ ነፃ የባንክአገልግሎት (ሸሪክ) ተጨባጭ ስኬቶች እንዲሁም የፋይናንስ ልህቀትንና አካታችነትን በተመለከተ የባንኩን ጉልህ ሚና የሚያሳዩ ስራዎች በኤክስፖው ላይ እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

ባንኩ በሙቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር በመመደብ የማሀበራዊ ኃላፊነት፤ የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ አሻራ እንዲሁም ለተለያዩ አገር በቀል የግብረሰናይ ድርጅቶች የገንዘብና የተለያዩ ድጋፎች እንደሚያደርግ የተጠቆመ ሲሆን በኤክስፖው ዳሽን ባንክ ማህበረሰብ ተኮር በሆኑ ተግባራት ላይ እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎች እንደሚተዋወቁና የስራ ሃሳብ ፈጠራን ለመደገፍ ይፋ ያደረጋቸውን አገልግሎቶችና ፕሮጀክቶች ለጎብኚዎች ያካፍላል ተብሏል።

ከ30 ዓመት በፊት በ11 መሥራቾች የተቋቋመው ዳሽን ባንክ በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ ከ900 በላይ ቅርንጫፎች፣ ከ8 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች፤ ከ2.2 ሚሊዮን በላይ የሱፐር አፕ ተጠቃሚ ደንበኞች ከ19 ሺህ በላይ ቋሚና ጊዜያዊ ሰራተኞች እንዳሉት ተጠቁሟል።

ከሚያዚያ 15 እስከ ሚያዚያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለዘጠኝ ቀናት በሚቆየው በዚህ ኤክስፖ የዳሽን ባንክን አመሰራረትና የሶስት አስርት ዓመታት ጉዞ የሚገልፁ አውደ ርዕዮችና ከዳሽን ባንክ ጋር አብረው የሚሰሩ የተለያዩ ተቋማት ምርትና አገልግሎቶች እንደሚቀርቡ ተገልጿል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories