በአለምሰገድ እስጢፋኖስ
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያን በአለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ወገን እየተከታተሉ የሚገኙት አልቫሮ ፒሪስ በቅርቡ ወደ አለም የብድር ስርአት ወደ መጣችው እና የአለም ባንክ እና IMF አባልነት የተመለሰችው ቬንዙዌላ ልኡክን ለመምራት መመረጣቸው እየተዘገበ ነው።
በዚህም አሁን የያዙት ሃላፊነት በሌላ የሚተካ ይሆናል።
ቬንዙዌላ እኤአ ከ2017 ጀምሮ በውጭ ያለባትን እዳ ያለመክፈል ሁኔታ/default ውስጥ የገባች ሲሆን ከ2019 ጀምሮ ደግሞ ከIMF እና የአለም ባንክ አባልነቷ ታግዳ ቆይታ ነበር።
አሁን ግን የእዳ ሽግሽግ ተደርጎላት ወደ አለም የገንዘብ ስርአት መመለስ እንደምትፈልግ ነው የተገለፀው።
በመሆኑም ፒሪስ የሚወስዱት ሃላፊነት ቀላል እንደማይሆንላቸው ነው የሚጠበቀው።SECO


