By EBV Staff Writer
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ይፋ በተደረገው 24ኛው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ውጤት የኢትዮጵያ ባንኮች በጨረታው ላይ ያሳዩት ተሳትፎና የጨረታ ዋጋ ከቀደመው ዙር ጋር ሲነጻጸር መቀነሱ ተስተውሏል።
በዚህ ዙር 14 ባንኮች ብቻ በጨረታው የተሳተፉ ሲሆን፣ በቀደመው ጨረታ 16 ባንኮች ተሳትፈው ነበር።
ብሔራዊ ባንኩ 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለጨረታ ያቀረበ ሲሆን በባንኮቹ የቀረበው አጠቃላይ ጥያቄ 160.5 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል።
በጨረታዎች ከፍተኛ ሆኖ የቀረበው ዋጋ 157 ብር ለአንድ ዶላር ሲሆን፣፣ ዝቅተኛው ደግሞ 152 ብር ለአንድ ዶላር ቀርቧል። ከ14ቱ ተሳታፊ ባንኮች ውስጥ 9ኙ የውጭ ምንዛሬ ድልድል ማግኘት ችለዋል።
የጨረታው ውጤት ባንኮች ለውጭ ምንዛሬ ጨረታ ለመካፈል የሚያሳዩት ፍላጎት በትንሹም ቢሆን የቀነሰ ነው። ከቀደመው ጨረታ ጋር ሲነጻጸር ለአንድ ዶላር የቀረበው ከፍተኛ ዋጋ በ1 ብር ዝቅ ብሏል፤ ይህም በውጭ ምንዛሬ ገበያ ያለው የፍላጎት ጫና በተወሰነ ደረጃ እየቀነሰ መሆኑን ቢያሳይም፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት አሁንም ተግዳሮት ሆኖ እንደቀጠለ ያሳያል።@seco


